Fana: At a Speed of Life!

አንድነት የመኪና ማቆሚያ ፕሮጄክት ከነገ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት ነጻ አገልግሎት ይሰጣል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አንድነት የመኪና ማቆሚያ ፕሮጄክት ከነገ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት የነጻ አገልግሎት እንደሚሰጥ የፕሮጀክቱ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡
 
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው ዕለት አንድነት የመኪና ማቆሚያ ፕሮጄክትን መርቀው ስራ አስጀምረዋል፡፡
 
በዚህ መሰረትም አንድነት የመኪና ማቆሚያ ፕሮጄክት ከነገ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት የነጻ አገልግሎት እንደሚሰጥ የፕሮጀክቱ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡
 
ከሳምንት በኋላም ደንበኞች አስፈላጊውን ክፍያ በመፈጸም አገልግሎቱን የሚያገኙ ይሆናል ነው የተባለው፡፡
 
ፕሮጄክቱ መጀመሪያ ወለል ላይና ከታች ባሉ አራት ተከታታይ የምድር ወለሎች አውቶቡሶችን ጨምሮ በአጠቃላይ ከ1ሺህ 20 በላይ ተሸከርካሪዎችን በአንድ ጊዜ ማስተናገድ እንደሚችል ተመላክቷል፡፡
 
በተጨማሪም አምፊ ቴዓትር፣ ባሕላዊ ምግብ ቤቶች፣ ሱቆችና ሌሎች መዝናኛዎችን ያካተተ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.