Fana: At a Speed of Life!

ፈረንሳይ ፖላንድን በማሸነፍ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቀለች

አዲስ አበባ፣ህዳር 25፣2015 (ኤፍ ቢሲ) በኳታር ዓለም ዋንጫ ፈረንሳይ ፖላንድን 3 ለ 1 በማሸነፍ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅላለች፡፡

በአልቱማም ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የፈረንሳይን የማሸነፊያ ጎሎች ኦሊቪዬር ጂሩ እና ኬሊያን ምባፔ አስቆጥረዋል፡፡

የፖላንድን ብቸኛ ጎል ሮቤርቶ ሌቫዶቭስኪ በተጨማሪ ሰዓት በፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥሯል፡፡

ኦሊቪዬ ጂሩ በዛሬው ጨዋታ ጎል ማስቆጠሩን ተከትሎ በ52 ጎሎች የፈረንሳይ የምንጊዜም ጎል አግቢነት ክብረወሰኑን  ከቴሪ ሄነሪ ተረክቧል፡፡

እንዲሁም ሁለት ጎሎችን ያስቆጠረው ኬሊያን ምባፔ ከ24 ዓመቱ በፊት በዓለም ዋንጫው ዘጠኝ ጎል ያስቆጠረ የመጀመሪያው ተጫዋች መሆን ችሏል፡፡

ከዚህ በፊት የብራዚሉ ፔሌ ከ24 ዓመት በፊት ሰባት ጎል ያስቆጥረ ብቸኛ ተጫዋች ሲሆን÷ይሄው ክብረወሰን በኬሊያን ምባፔ ተሻሽሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.