Fana: At a Speed of Life!

በጥሎ ማለፉ ጃፓን ከክሮሺያ እንዲሁም ብራዚል ከደቡብ ኮሪያ ይጫወታሉ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም ዋንጫው የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ዛሬም ቀጥለው ይካሄዳሉ።

በዛሬው የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ሁለቱ የእስያ ተወካዮች ጃፓን እና ደቡብ ኮሪያ ከክሮሺያ እና ብራዚል ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ማምሻውን 12 ሰአት በሚካሄድ ጨዋታ ጃፓን ከክሮሺያ ይገናኛሉ።

በምድብ 5 ስፔንን አስከትላ ያለፈችው ጃፓን ከ2018ቱ የዓለም ዋንጫ የፍጻሜ ተፋላሚ ክሮሺያ ጋር የምታደርገው ጨዋታ ከወዲሁ ተጠባቂ ሆኗል።

በሌላ ጨዋታ ምሽት 4 ሰአት ላይ ኮከቧ ኔይማር ወደ ልምምድ የተመለሰላት የዋንጫ ተገማቿ ብራዚል ከሌላኛዋ የእስያ ተወካይ ደቡብ ኮሪያ ጋር ትጫወታለች።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.