Fana: At a Speed of Life!

የምሁራን የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)”ለኢትዮጵያ ልዕልና የምሁራን ሚና” በሚል መሪ ቃል ከመላ ሃገሪቱ የተውጣጡ ምሁራን ውይይት እየተካሄደ ነው።

ውይይቱ በኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ እና በአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት የተጀመረ ሲሆን ከፍተኛ የምርምር ተቋማት ባለሙያዎች እና ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ምሁራን እየተሳተፉ ይገኛል።

የኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ብርሃነመስቀል ጠና በመክፈቻው እንደተናገሩት፥ በሃገራችን ጉዳይ ምሁራን የተጣለባቸው አደራ እጅግ የገዘፈ ቢሆንም የሚጠበቅባቸውን ያህል እየተወጡ አይደለም።

ምሁራን የልዩነት ሃረግ በመምዘዝ የአብሮነት እሴቶችን ከሚሸረሽሩ ጉዳዮች በመውጣት ለዘላቂ ሰላም እና ለህዝብ ጥቅም መቆም አለባቸው ብለዋል፡፡

ምሁራን ተቀራርበው ያለመስራት እና አንድ በሚያደርጉ ጉዳዮች የመተባበር ችግር እንዳለባቸው በማንሳትም፥ የአብሮነት እሴትን ለመሸርሸር የሚሰሩትን መታገል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ኢትዮጵያ በምሁራኖች ትከበር ዘንድ በሃገራዊ፣ ቀጠናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ከምሁራን እና ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምን ይጠበቃል በሚል ርዕስ ላይ በቀጣይ  ውይይት ይካሄዳል።

በምንይችል አዘዘው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.