Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ሁለት ሕጻናትን በአሰቃቂ ሁኔታ በገደለችው ሕይወት መኮንን ላይ የሞት ቅጣት ተወሰነ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ አራብሳ አካባቢ ነሐሴ 26 ቀን 2014 ዓ.ም ሁለት ሕጻናትን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድላለች የተባለችው ተከሳሽ ሕይወት መኮንን በሞት ቅጣት እንድትቀጣ ተወስኖባታል፡፡

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ ከባድ ግድያ እና የውንብድና ጉዳዮች ችሎት ዛሬ ባዋለው ችሎት፥ ከዚህ ቀደም ሁለት ሕጻናትን በመግደል ወንጀል በተከሰሰችው ሕይወት መኮንን ላይ የሞት ቅጣት ወስኗል፡፡

ተከሳሽ ሕይወት መኮንን በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ቦሌ አራብሳ የጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ በቤት ሠራተኛነት ተቀጥራ በምትሠራበት መኖሪያ ቤት ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ነሐሴ 26 ቀን 2014 ዓ.ም የሁለት ሕጻናትን ሕይወት በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲያልፍ አድርጋለች በሚል ከባድ የግድያ ወንጀል ክስ ቀርቦባት ነበር፡፡

በተጨማሪም ተከሳሽ የሟቾችን የቤተሰብ ሰነድ ማስረጃዎች በማጥፋት ወንጀል ተደራራቢ ክስ መከሰሷ ይታወቃል፡፡

በአወል አበራ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.