Fana: At a Speed of Life!

17ኛው የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 17ኛው የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ በሻሸመኔ ከተማ እየተከበረ ይገኛል፡፡

በዓሉ በተለያዩ ስነ-ስርዓቶች ነው እየተከበረ የሚገኘው፡፡

በመድረኩ የተለያዩ ክልሎች እና ከተሞች አፈ ጉባኤዎች፣ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ፣የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ አባገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ሰአዳ አብዱራህማን እንደገለፁት÷ህብረ ብሄራዊ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን ለማጠናከር ስራዎች እየተሰሩ ነው።

ሕብረ ብሔራዊ ፌዴራላዊ ስርዓት ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ አንጻር የተሻለና የሚነሱ ቅሬታዎችን በዴሞክራሲያዊ ውይይት ለመፍታት ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለውም ገልጸዋል።

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትም በተለያየ መልኩ ሕብረ ብሔራዊ ፌዴራሊዝምን የሚያጎለብቱና የሕዝቦችን አንድነት የሚያጠናክሩ ተግባራትን እያከናወነ ነው ብለዋል።

እንደ አፈ ጉባኤዋ ገለጻ የብሔር ብሔረሰቦች ቀን መከበሩ ሕዝቦች ባህላቸውንና ማንነታቸውን እንዲያስተዋውቁና እርስ በእርስም እንዲተዋወቁ ያደርጋል።

የሻሸመኔ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አዳነ ተክለጊዮርጊስ በበኩላቸው÷ የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በክልል ደረጃ በሻሸመኔ መከበሩ በከተማዋ የሚኖሩ ሕዝቦችን አንድነት የሚያጠናክር መሆኑን ጠቅሰዋል።

በጂብሪል ሀሰን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.