Fana: At a Speed of Life!

በፀረ-ሙስና ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በፀረ-ሙስና ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡
 
በውይይት መድረኩ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች ፣ ባለድርሻ አካላት ፣ የሚዲያ እና ኪነ ጥበብ አካላት እንዲሁም የሲቪል ማህበረሰብ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል፡፡
 
ኮሚሽኑ በኢትዮጵያ እየተካሄደ የሚገኘውን የፀረ-ሙስና ትግል ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ የሚያግዝ ሀገር አቀፍ የፀረ-ሙስና አማካሪ ምክር ቤት ለማቋቋም የፀረ-ሙስና ረቂቅ ፖሊሲ ማዘጋጀቱ ተገልጿል፡፡
 
በዚህ ረቂቅ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በሚደረገው ውይይትም አስፈላጊ ግብዓቶች ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.