Fana: At a Speed of Life!

የሱዳን ወታደራዊ እና ሲቪል ኃይሎች የፖለቲካ ቀውሱን ለማስቆም ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሱዳን ወታደራዊ እና ሲቪል ኃይሎች የፖለቲካ አለመግባባቱን ለማስቆም እና በሲቪል የሚመራ የሽግግር መንግስት ለመመስረት የሚያስችል ስምምነት በትናንትናው ዕለት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱ በሱዳን ጦር ሃይሎች አዛዥ ጀኔራል አብዱልፈታህ አል-ቡርሃን እና በሲቪል አመራሮች የነጻነት እና የለውጥ ሃይሎች ተብሎ በሚጠራው አካል መካከል ተፈርሟል።

በስምምነቱ ሀገሪቱን ወደ ምርጫ የሚመራ አዲስ የሲቪል የሽግግር መንግስት ለመመስረት ቃል የተገባ ሲሆን፥ በሱዳን የተቋረጠውን የዴሞክራሲ ሽግግር ሂደት ያሳልጣል ተብሎለታል።

በፈረንጆቹ ጥቅምት 25 ቀን 2021 ጀኔራል አል-ቡርሃን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማወጅ ሉዓላዊ ምክር ቤቱን እና የሽግግር መንግስቱን ከበተኑ በኋላ ሱዳን በፖለቲካዊ ቀውስ ውስጥ እንደምትገኝ የሲ ጂ ቲ ኤን ዘገባ አመላክቷል።

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ዋና ከተማዋ ካርቱም እና ሌሎች ከተሞች ሥርዓቱ ወደ ሲቪል አገዛዝ ይመለስ የሚሉ ተቃውሞዎችን ማስተናገዳቸውም ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.