Fana: At a Speed of Life!

ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ከውጭ የመጡ ተጓዦች ለ14 ቀናት የሚያሳልፉበትን ስፍራ ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 21 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ አቃቤ ህግ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ከውጭ የመጡ ተጓዦች ለ14 ቀናት በለይቶ ማቆያ የሚያሳልፉበትን ስፍራ ጎበኙ።

ወይዘሮ አዳነች አቅም ሳይኖራቸው በመንግስት ወጪ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርሲቲ የሚቆዩባቸውን ቦታዎች ነው የጎበኙት።

በጉብኝቱ ላይ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትሯ ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም ተካፍለዋል።

በዚህ ወቅትም በተዘጋጁ ቦታዎች ያለውን ሁኔታና አቅርቦት ጋር የተገናኙ ጉዳዮችን በተመለከተ በስፍራው ካሉ ሃላፊዎች ጋር ተነጋግረዋል።

በሀብታሙ ተክለስላሴ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.