Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ተፈራ የጃፓን ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጃፓን የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈራ ደርበው ጃፓን ከሚገኙ 13 ኩባንያዎች ሃላፊዎች ጋር በኢትዮጵያ ባሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች ዙሪያ መክረዋል፡፡

በውይይታቸውም ኢትዮጵያ እና ጃፓን ረጅም ዘመን ያስቆጠረ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን አንስተዋል፡፡

በቀጣይም ሀገራቱ በንግድ እና ኢንቨስትመንት ዘርፍ ያላቸውን ግንኙነት እና ትብብር ይበልጥ ማጠናከር እንደሚገባ ነው ያስረዱት፡፡

አምባሳደር ተፈራ በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች እምቅ እና ያልተነኩ የኢንቨስትመንት አማራጮች መኖራቸውን ለተሳታፊዎቹ አብራርተዋል፡፡

በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ህግ፣ ማበረታቻዎች፣ በአየር ጸባይ ፣ በመሰረት ልማት ቅድሚያ በሚሰጣቸው ዘርፎች እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይም ገላጻ አድርገዋል፡፡

አምባሳደሩ የጃፓን ኩባንያዎች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ተሳታፊዎቹ በበኩላቸው በኢትዮጵያ ባሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች ዙሪያ ሰፊ እና ጠቃሚ መረጃ ማግኘታቸውን ጠቅሰው÷በቀጣይ ኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት መዳረሻ ለማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ጠቁመዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.