Fana: At a Speed of Life!

ቡና ባንክ በበጀት ዓመቱ መጨረሻ ከግብር በፊት 1ነጥብ 19 ቢሊየን ብር አተረፈ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቡና ባንክ በበጀት ዓመቱ መጨረሻ ከግብር በፊት 1 ነጥብ 19 ቢሊየን ብር ማትረፉን እና ከ27 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ተቀማጭ ገንዘብ መሰብሰብ መቻሉን ገልጿል።

የባንኩ ተቀማጭ ገንዘብ መጠንም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ6 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ማደጉን የቦርዱ ሊቀመንበር አምባሳደር ዓለማየሁ ሰዋገኝ ጠቁመዋል፡፡

በዚህም የባንኩን አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን በ32 ነጥብ 8 በመቶ ከፍ በማድረግ 27 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር እንዳደረሰው ተነግሯል።

ከዚህ ውስጥ የቁጠባ ሂሳብ ተቀማጭ 77 ነጥብ 8 በመቶ የሚሆነውን ከፍተኛ ድርሻ እንደያዘ ነው ባንኩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መረጃ የተመላከተው።

ባንኩ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ፣ የሩሲያ ዩክሬን ጦርነትና በሀገሪቱ ተፈጥሮ የነበረው የጸጥታ ችግር በአገር ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ ያሳደሩትን መቀዛቀዝ ተቋቁሞ በአትራፊነት መቀጠል ስለመቻሉም ተገልጿል፡፡

ይህም ለባንኩ ባለአክሲዮኖችና ለአጠቃላይ ሰራተኞቹ የሚያበረታታ ውጤት ነው ተብሏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.