Fana: At a Speed of Life!

ከልዋን ፣ያሎ እና ቢሶበር ከተሞች በድጋሜ  የኤሌክትሪክ ኃይል አገኙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጦርነት ምክንያት ኃይል ተቋርጦባቸው የነበሩት ከልዋን ፣ያሎ እና ቢሶበር ዳግም የኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘታቸውን የአፋር ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡

የአግልገሎቱ ስራ አስፈፃሚ ያሲን አሌ እንደገለፁት÷አገልግሎቱን እንደገና ለመመለስ በተደረገ እልህ አስጨራሽ የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ጥገና እነዚህ አካባቢዎች ዳግም የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡

አካባቢዎች ከአላማጣ የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያ የሚያገኙ በመሆናቸው ለረጅም ጊዜ ኃይል ተቋርጦቦቸው መቆየቱንአስረድተዋል፡፡

በጦርነቱ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው የነበሩ የመከከለኛና የዝቅተኛ የኤሌክትሪክ መስመሮችን እና ትራንስፈርመሮች እንደገና በመጠገን አገልግሎቱ መመለስ መቻሉን  አብራርተዋል፡፡

በመጨረሻም በክልሉ በኪልበቲ ረሱ የሚገኙ ወረዳዎች ዳግም ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ ጥገና ለማድረግ የሚያስችል ጥናት ተጠናቆ ግብአት የማሟላት ስራ እየተሰራ ነው ሲሉ ስራ አሰፈፃሚው መናገራቸውን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.