Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ በኢትዮጵያ ከዩኔስኮ ተወካይ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ከአዲሷ የተመድ የትምህርት፣ የሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በአፍሪካ ህብረትና በተመድ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ተጠሪ እንዲሁም በኢትዮጵያ የድርጅቱ ተወካይ ሪታ ቢሶነዝ ጋር ተወያዩ።

ተጠሪዋ ድርጅቱ በአፍሪካ ከ2022 እስከ 2029 ሊተገብር ባቀደው አዲስ ስትራቴጂ ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በተጨማሪም የ “ሣኅለወርቅ የትምህርት የወደፊት እጣ ፈንታ ሪፖርት” ዙሪያ መወያየታቸውን የፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

ፕሬዚደንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ለሁለት አመታት የትምህርት የወደፊት እጣ ፈንታ ዓለም አቀፍ ኮሚሽን ሰብሳቢ እንደነነበሩ ይታወሳል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.