Fana: At a Speed of Life!

ምሁራን ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ዘላቂ ሰላም ተገቢውን ሚና መጫወት አለባቸው- ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምሁራን የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ በመገንዘብ ለሉዓላዊነቷ እና ለዘላቂ ሰላሟ ተገቢውን ሚና መጫወት አለባቸው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡
 
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለኢትዮጵያ ልዕልና የምሁራን ሚና በሚል መሪ ቃል ከመላ ሀገሪቱ የተውጣጡ ምሁራን በተሳተፉበት የውይይት መድረክ ላይ ተገኝተዋል፡፡
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ ምሁራን የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ በመገንዘብ ለሉዓላዊነቷ እና ለዘላቂ ሰላሟ ተገቢውን ሚና መጫወት አለባቸው ብለዋል፡፡
 
የሁላችንም ችግሮች የሚፈቱት በሁላችንም የትብብር ትግል ነው ሲሉም ገልጸዋል።
 
ዕውቀትና አዋቂ የሚከበርበት ማኅበረሰብ ለመገንባት እንድንችል መንግሥት እና ምሁራን ተቀራርበው ለአንድ ሀገር መሥራት አለባቸውም ነው ያሉት፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.