Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል በ832 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የለማ ስንዴን መሰብሰብ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በ832 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የለማ ስንዴን መሰብሰብ መጀመሩን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታውቋል፡፡
 
የሰብል ስብሰባ መርሐ ግብሩ በምስራቅ ጎጃም ዞን ባሶ ሊበን ወረዳ የተጀመረ ሲሆን÷ ስብሰባው በኮምባይነር እየተከናወነ እንደሚገኝ ተመላክቷል፡፡
 
በመርሐ ግብሩ የተገኙት የክልሉ ግብርና ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ሃይለማርያም ከፍያለው÷ አሁን ላይ ግብርናውን ወደ ሜካናይዜሽን መማጣት ግዴታ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
 
በክልሉ በዘንድሮው ዓመት የለማውን 832 ሺህ ሄክታር የስንዴ ማሣ በፍጥነት ለመሠብሠብ በክልሉ ካሉት በተጨማሪ ከሌሎች አካባቢዎች በኪራይ ገብተው እንዲያገለግሉ ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑንም ገልጸዋል።
 
ሰብል በኮምባይነር መሠብሰቡ ማሳን ለመስኖ ልማት በፍጥነት ለማድረስ አጋዥ እንደሆነ የተናገሩት ሃላፊው÷ ምርታማነቱንም ከ42 ኩንታል ወደ 53 ኩንታል ማድረስ ማስቻሉን ጠቁመዋል።
 
አርሶ አደሮች በበኩላቸው ሰብላቸውን በኮምባይነር ለመሰብሰብ በክላስተር መስራታቸው እንደጠቀማቸው አንስተው÷ ምርት እንዳይበላሽና በፍጥነት ለመሠብሰብም ጠቀሜታው የላቀ መሆኑን ገልጸዋል።
 
በበላይነህ ዘላለም
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.