Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ከተመድ የሥርዓተ ምግብ ከፍተኛ ሃላፊ ጌርዳ ቨርበርግ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝት በማድረግ ላይ ከሚገኙትን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሥርዓተ ምግብ ከፍተኛ ሃላፊ ጌርዳ ቨርበርግ ጋር ተወያይተዋል፡፡
 
በውይይታቸውም በኢትዮጵያ በምግብና ሥርዓተ ምግብ፣በምግብ ሥርዓተ ትራንስፎርሜሽን እንዲሁም በሰቆጣ ቃል ኪዳን አተገባበር ላይ በትኩረት መክረዋል፡፡
 
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ÷ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2023 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሚያዘጋጀውን የሥርዓተ ምግብ ዓለም አቀፋዊ ጉባኤ የማዘጋጅት ፍላጎት እንዳላት ገልጸዋል።
 
ጌርዳ ቨርበርግ በበኩላቸው÷ መንግሥት በሥርዓተ ምግብ ሥራዎች አተገባበር ያለውን ቁርጠኝነት በተለይም በሚኒስቴር መሥራያ ቤቶች መካከል ያለው ቅንጅታዊ አሰራር እንዳስደነቃቸው ተናግረዋል፡፡
 
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ የሀገር አቀፉ የሥርዓተ ምግብ ሻምፒዮን እንዲሆኑ ጥያቄ ማቅረባቸውንም ከፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.