Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮ-ሩሲያ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 27 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 8ኛው የኢትዮ-ሩሲያ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል፡፡

በመድረኩ ማስጀመሪያ ላይ መልክት ያስተላለፉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር በለጠ ሞላ ኢትዮጵያ እና ራሽያ ያላቸውን ጠንካራ ታሪካዊ ግንኙነት አንስተዋል።

ሩሲያ በሳይንስ፣ በትምህርትና ሌሎች ዘርፎች ለኢትዮጵያ እያደረገች ያለውን ድጋፍ በማመስገን በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል።

መድረኩ ሳይንስ፣ ቴክኒክ፣ ኢኮኖሚ እና የንግድ ትብብር እንዲሁም የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶች የሚያጠናክሩበት እንደሚሆን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ተግባራዊ እያደረገች ባለው የአገር በቀል ምጣኔ ሀብት በማዕድንና ሌሎች ዘርፎች ያሉ አማራጮች ላይ የራሺያ ባለሀብቶች ኢንቨስት እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል።

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአውሮፓ እና አሜሪካ ጉዳዮች ዳሬክተር ጀነራል አምባሳደር እሸቴ ጥላሁን÷ ዛሬ የተጀመረዉ የሁለቱ ሀገራት የጋራ ሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባ ከመደበኛ የሁለትዮሽ ስብሰባ ይልቅ በምንግዜም የወዳጅ ሀገራት የሚደረግ ስብሰባ ነው ብለዋል ።
በኢትዮጵያ ሩሲያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴርኪን በበኩላቸው÷ዛሬ የተጀመረው የሁለቱ ሀገራት የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ሁለቱ ሀገራት ለሚያከናዉኗቸዉ የኢኮኖሚ እና የኢንቨስትመንት ትብብሮችን ለማሳደግ ከፍትኛ አቅም እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡
በሚኒስትሮቹ የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ አገራቱ በጋራና በተናጠል ሊያከናውኗቸው ያቀዷቸው ጉዳዮች በማቅረብ ከዚህ ቀደም የገቧቸውን ስምምነቶች ውጤት ይገመግማሉ።
እንዲሁም የተለያዩ ስምምነቶች ይደረሳሉ ተብሎም ይጠበቃል ።
በፀጋዬ ወንድወሰን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.