Fana: At a Speed of Life!

በውርስ ከተያዙ ተሽከርካሪዎች ሰሌዳ እየፈታ ለሕገ ወጥ ተግባር ሲገለገል የነበረ ግለሰብ እጅ ከፍንጅ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ ቅርንጫፍ የጉምሩክ የውርስ መጋዘን ጸሐፊ በውርስ ከተያዙ ተሽከርካሪዎች ሰሌዳ እየፈታ ለሕገወጥ ተግባር ሲገለገልበት እጅ ከፍንጅ መያዙን ፖሊስ ገለጸ፡፡

ተጠርጣሪው በውርስ ከተያዙ ተሽከርካሪዎች የሰሌዳ ቁጥር እየፈታ ለደላሎችና በሕገወጥ ተግባር ላይ ለተሰማሩ ሰዎች በ15 ሺህ ብር ሲያከራይ እንደነበር ተጠቅሷል፡፡

ይህን የሰሌዳ ቁጥር በመጠቀም ከሶማሌ ላንድ ሠነድ አልባ ተሽከርካሪዎች በሕገወጥ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ  መደረጉን የፌደራል ፖሊስ መረጃ አመላክቷል፡፡

ተጠርጣሪው በውርስ ከተያዘ ተሽከርካሪ ሰሌዳ ፈትቶ ሲሰጥ እና 15 ሺህ ብር ሲቀበል በድሬዳዋ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ እጅ ከፍንጅ ተይዞ ምርመራ እየተካሔደበት ነው፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.