Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል ባለፉት ሶስት ሳምንታ ከውጭ ሀገራት ወደ ክልሉ የተመለሱ ዜጎች በየአካባቢያቸው ለሚገኝ የመንግስት የጤና ተቋም ሪፖርት እንዲያደርጉ አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአማራ ክልል ባለፉት ሶስት ሳምንታ ከውጭ ሀገራት ወደ ክልሉ ክልል የተመለሱ ዜጎች በየአካባቢያቸው ለሚገኝ የመንግስት የጤና ተቋም ሪፖርት እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ሰጠ።

በአማራ ክልል የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት መግለጫ አውጥቷል።

በመግለጫውም ባለፉት ሶስት ሳምንታ ከውጭ ሀገራት ወደ ሀገር ቤት የተመለሱ እና በአማራ ክልል ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች በአስቸኳይ በየአካባቢያቸው ወደሚገኝ የመንግስት የጤና ተቋም ሪፖርት እንዲያርጉ እና ራሳቸውን እና ያገኟቸውን ሠዎች እንዲያቀርቡ አሳስቧል።

ለክልሉ የገጠር ነዋሪዎች በሙሉ ያጋጠመው ችግር አስቸጋሪ መሆኑን በመረዳት ለግብይትም ሆነ ለሌላ ማህበራዊ ጉዳዮች ወደ ከተማ የሚያደርጉትን ጉዞ በማቆም ባሉበት ሆነው ራሳቸውን እንዲጠብቁ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

የክልሉ ነዋሪዎች አሁን ካለው የወረርሽኙ አሣሣቢ ሁኔታ አንፃር እንደ አስፈላጊነቱ ታይቶ በክልሉ ውስጥ የሚደረግ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲቆም ትዕዛዝ ሊሠጥ ይችላልም ነው ያለው።

ከዚህ አንጻርም ይኸንኑ በማወቅ ወደ ቋሚ የመኖሪያ (መቆያ) ቦታቸው ላይ በመሆን ከመንግስት የሚሠጠውን ትዕዛዝ በትኩረት እንዲጠባበቁ ኮሚቴው ማሳሰቡን የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.