Fana: At a Speed of Life!

በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው የጤና ተቋማት ከ21 ሚሊየን ብር በላይ የሚሆን የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2015፣ (ኤፍ ቢ ሲ) በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት ደርሶባቸው ለነበሩ የጤና ተቋማት የሚውልና ከ21 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የህክምና ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደርጓል።

ድጋፉን ያደረገው ጉድዊል የተሰኘ አገር በቀል ድርጅት ሲሆን÷ ድጋፉም ማይክሮስኮፕ፣ ዘመናዊ ኮምፒዩተሮችና ሌሎች የህክምና መገልገያዎች መሆኑ ተገልጿል።

በድጋፉ ሰሜን ሸዋ፣ ደቡብና ሰሜን ወሎ እንዲሁም አፋር ክልል የሚገኙ በአጠቃላይ 19 የጤና ተቋማት ተጠቃሚ ይሆናሉ ሲሉ የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ወንድወሰን ደስታ ተናግረዋል።

የህክምና ቁሳቁስ ድጋፉ የጤና ተቋማቱ ወደ ቀደመ አገልግሎታቸው እንዲመለሱና ክፍተታቸውን እንዲሞሉ ያስችላቸዋልም ነው ያሉት።

የደሴ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ ዶክተር ሀይማኖት አየለ በበኩላቸው÷ የተደረገው ድጋፍ የጤና ተቋማቱን አገልግሎት በማሻሻል ረገድ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።

በአንድነት ናሁሰናይ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.