Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል የኤሌክትሪክ አገልግሎት ዳግም እንዲጀመር ቅድመ ዝግጅት ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል የኤሌክትሪክ አገልግሎት ዳግም ለማስጀመር ቅድመ ዝግጅት መጀመሩን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡

የአገልግሎቱ ከፍተኛ ሥራ አመራር በትግራይ ክልል የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቱ ላይ የደረሰውን ጉዳት በመለየት አስቸኳይ ጥገና ተደርጎ በአጭር ጊዜ ህብረተሰቡ የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዲያገኝ በሚቻልበት ሂደት ላይ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

በዚህም መሰረት የተለያዩ የቴክኒክ ባለሙያዎች ቡድን የተዋቀረ ሲሆን÷ ከነገ ጀምሮ ለጥገና ሥራው የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን በማሟላት ከሰሞኑ ወደ ክልሉ እንደሚሰማሩ የአገልግሎቱ መረጃ አመላክቷል፡፡

በአጭር ጊዜ የጥገና ሥራውን በማጠናቀቅ ህብረተሠቡ የተቋረጠውን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ዳግም እንዲያገኝ በትኩረት እንደሚሠራም ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.