Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ከኢጋድ አባል ሃገራት መሪዎች ጋር በቪዲዮ ኮንፈረንስ ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 21 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) አባል ሃገራት መሪዎች ጋር በቪዲዮ ኮንፈረንስ ተወያዩ።

በውይይታቸው ወቅትም ኮቪድ19 በዓለም አቀፍ ደረጃ እያስከተለ የሚገኘውን ፈታኝ ሁኔታ ለመቋቋም የጋራ አመራር አስፈላጊ እንደሆነ መስማማታቸውን በፌስ ቡክ ገጻቸው አስፍረዋል።

ቫይረሱ በጤና ሥርዓታችን እና በኢኮኖሚያችን ላይ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ በየግላችን ለመቋቋም ከባድ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ሁኔታው ከአሁኑ እንደ ቱሪዝም ባሉና በፍጥነት በማደግ ላይ ያሉ የኢንዱስትሪ ዘርፎች ላይ ጫና ማሳደሩንም ጠቅሰዋል።

ስለዚህ ሁኔታውን ለመቋቋም በጋራ ድጋፍን ማፈላለግ፣ እያንዳንዳችን በቀላሉ ልናገኛቸው የምንችላቸውን ግብአቶች መጋራት እንዲሁም በቅርበት ሆኖ ልምድ መለዋወጥ መፍትሔ መሆኑን ጠቁመዋል።

ሃገራት ያስመዘገቡት የኢኮኖሚ ዕድገት ለጉዳት የተጋለጠ በመሆኑ ሁኔታውን በአሸናፊነት ለመወጣት በጋራ አመራር እና በተቀናጀ ተግባር ብቻ መሆኑንም አንስተዋል።
ተስፋን መሰነቅ፣ በዕቅድ መመራትና ተባብሮ መሥራት እንደሚያስፈልግም አጽንኦት ሰጥተዋል።

በተመሳሳይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከደቡብ ኮሪያው ፕሬዚዳንት ጋር  ሙን ጄ ኢን ጋር  ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ደቡብ ኮሪያ የየኮሮና ቫይረስ ጉዳት እንዳያስከትል የሰራችው ስኬታማ ስራ የኮቪድ19ን ሥርጭት እንዴት በቁርጠኝነት መግታት እንደሚቻል አርአያ ናት ብለዋል።

ኢትዮጵያ ተሞክሯዎቹን በምን መንገድ ልትጠቀምበት እንደምትችል እንዲሁም ደቡብ ኮሪያ አስፈላጊ የሕክምና መገልገያዎች በመለገስ ድጋፍ በምታደርግበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸውን በፌስቡክ ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.