Fana: At a Speed of Life!

የመቀሌ የኤሌክትሪክ ኃይል መስመር ከብሔራዊ የኃይል ቋት ጋር ተገናኘ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከብሔራዊ የኃይል ቋት ጋር ተቋርጦ የቆየው የመቀሌ ከተማ ኤሌክትሪክ ኃይል ከብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል (ግሪድ) ጋር መገናኘቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።

የመቀሌ ከተማ ኤሌክትሪክ ኃይል ከአንድ ዓመት በላይ ከብሔራዊ የኃይል ቋት ጋር ተቋርጦ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

መስመሩ ከብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል ጋር የተገናኘው÷ ከአላማጣ መኾኒ በተዘረጋው የባለ 230 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ጥገና ከተጠናቀቀ በኋላ መሆኑን ተገልጿል፡፡

መስመሩ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ÷ በክልሉ ኤሌክትሪክን መልሶ ሥራ ለማስጀመር የተጀመረውን ሥራ ያፋጥናል መባሉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

እንዲሁም ከሁመራ እስከ ሽረ ድረስ የተዘረጋው የባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ጥገና መጠናቀቁ ተመላክቷል፡፡

ሆኖም ለሽረ ኃይል የሚሰጠው ከተከዜ እስከ አክሱም በተዘረጋው መስመር ስምንት ቦታዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማጋጠሙ ጥገናው ወደ ተከዜ የኃይል ማመንጫ ጣቢያ መቀጠሉ ነው የተገለጸው፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.