Fana: At a Speed of Life!

ቻይና በኢትዮጵያ በድርቅና ግጭት ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ድጋፍ እንደምታደርግ ገለፀች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በቅርቡ ቻይና በኢትዮጵያ በድርቅና ግጭት ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የምግብ ድጋፍ እንደምታደርግ በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ የኢኮኖሚ ካውንስለር ከ ያንግ ዪሃነግ ገለፁ፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር የኢኮኖሚ ትብብር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው በኢትዮጵያ ከቻይና ኤምባሲ የኢኮኖሚ ካውንስለር ከ ያንግ ዪሃነግ ጋር በሁለቱ ወዳጅ ሀገሮች የኢኮኖሚ ትብብርና ኢንቨስትመንት ጉዳዮች ላይ ተወያይዋል፡፡

በውይይቱ ወይዘሮ ሰመሪታ÷ የኢትዮጵያ መንግስት ከቻይና መንግስት ጋር ያለውን የኢኮኖሚ ትብብር አጠናክሮ ለመቀጠል በትኩረት እየሰራ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

የቻይና ኤምባሲ የኢኮኖሚ ካውንስለር ያንግ ዪሃነግ በበኩላቸው÷ ቻይና ከወዳጅ ሀገር ኢትዮጵያ ጋር ያላትን የኢኮኖሚ ትብብር አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠው በቅርቡም ቻይና በኢትዮጵያ በድርቅና ግጭት ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የምግብ ድጋፍ እንደምታደርግ ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም በቀጣይ ወራት ለኢትዮ-ጅቡቲና ለአዲስ አበባ ቀላል ባቡር አገልግሎት የሚውሉ መለዋወጫዎችና አስፈላጊ ቁሳቁሶች ድጋፍ ወደ ሀገር ውስጥ እንደሚገቡም የኢኮኖሚ ካውንስለሩ አስረድተዋል፡፡

በዚሁ የሁለትዮሽ ውይይት ወቅት የቻይና ኤምባሲ ለገንዘብ ሚኒስቴር የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችና የቢሮ መገልገያ ቁሳቁሶችን ማበርከቱን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.