Fana: At a Speed of Life!

ፖርቹጋል ስዊዘርላንድን በሰፊ ውጤት በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቀለች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፖርቹጋል ስዊዘርላንድን በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቀለች።

ምሽት አራት ሰዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ ፖርቹጋል ስዊዘርላንድን 6ለ 1 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፋለች።

ለፖርቹጋል ጎንሳሎ ራሞሰ በ17ኛው ፡ በ51ኛውና በ67ኛው ደቂቃዎች ላይ ባስቆጠራቸው ጎሎች ሃትሪክ ሲሰራ ቀሪዎቹን ሶስት ጎሎች ደግሞ ፔፔ በ33ኛው ፥ ራፋኤል ጉሬሮ በ55ኛው እንዲሁም ራፋኤል ሌዯ በጭማሪ ሰዓት ላይ አስቆጥረዋል።

የስዊዘርላንድን ብቸኛ ጎል ማኑኤል አካንጂ በ58ኛው ደቂቃ ላይ በስሙ አስመዝግቧል።

ቀደም ብሎ 12 ሰዓት ላይ በተደረገ ጨዋታ ሞሮኮ ስፔንን በመለያ ምት 3ለ0 በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን መቀላቀሏ ይታወሳ።

በዚህም መሰረት የፊታችን ቅዳሜ ሞሮኮ ፖርቹጋልን የምትገጥም ይሆናል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.