Fana: At a Speed of Life!

የክርስቲያኖ ሮናልዶ ቋሚ አሰላለፍ ውስጥ አለመግባት አዳዲስ የፖርቹጋል ኮከቦችን አስተዋውቋል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በስዊዘርላንዱ ጨዋታ የክርስቲያኖ ሮናልዶ ቋሚ አሰላለፍ ውስጥ አለመግባቱ አዳዲስ የፖርቹጋል ኮከቦች በመድረኩ እንዲታወቁ እድል ሰጥቷል፡፡

ትላንት ምሽት ፖርቹጋል ስዊዘርላንድን 6 ለ 1 ባሸነፈችበት ጨዋታ አሰልጣኝ ፈርናንዶ ሳንቶስ ክርስቲያኖ ሮናልዶን ተጠባባቂ ወንበር ላይ በማስቀመጥ በምትኩ የቤኔፊካውን አጥቂ ጎንዛሎ ራሞስን ወደ ሜዳ አስገብተዋል፡፡

የአሰልጣኙን ታክቲክ ውጤታማ ያደረገው ታዲያ በሮናልዶ ምትክ ወደሜዳ የገባው የ21 አመቱ አጥቂ ጎንዛሎ ራሞስ በአለም ዋንጫው ሀትሪክ በመስራት ፖርቹጋልን በቀላሉ ወደ ሩብ ፍፃሜ እንድታልፍ ማድረጉ ነው፡፡

እንደ ቢቢሲ ስፖርት ትንተናም ፖርቹጋል በቀላሉ ያሸነፈቸው የስዊዘርላንድ ተጫዋቾች ትኩረታቸውን ሮናልዶ ላይ አድርገው እንደነበር እና አሰልጣኝ ፈርናንዶ ሳንቶስ የአሰላለፍ ለውጥ ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው ብሏል፡፡

ደጋፊዎች ባደረጉት ጫና ሮናልዶ በ74ኛው ደቂቃ ወደ ሜዳ እንዲገባ ያደረጉት ፈርናንዶ ሳንቶስ ከጨዋታው በኋላ በሰጡት አስተያይት ከሮናልዶ ጋር ጥሩ ግንኙነት አለን ከ19 አመቱ ጀምሮ አውቀዋለሁ፣ ይህን ያደርግነው ለቡድን ውጤት ስንል ብቻ ነው ብለዋል፡፡

የ37 አመቱ አጥቂ በቅርቡ ከማንቼስተር ዩናይትድ ጋር በፈጠረው ውዝግብ እና ከእድሜ ጋር ተያይዞ ባሳየው የአቋም መዋዥቅ የአለም ተፅዕኖ ፈጣሪነቱን እየቀነሰበት ስለመሆኑ እየተገለፀ ይገኛል፡፡

የእግርኳስ አቢዮተኛዋ ፖርቹጋል ከትላንት ምሽቱ ጣፋጭ ድል መልስ ወደ ግማሽ ፍፃሜው ለማለፍ ከአፍሪካዊቷ ሞሮኮ ጋር የምተጫዎት ይሆናል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.