Fana: At a Speed of Life!

የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ሳዑዲ ዓረቢያን ሊጎበኙ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ በሳዑዲ ዓረቢያ የሶስት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው፡፡

ጉብኝቱ ሳዑዲ ዓረቢያ ከአሜሪካ ጋር ያላት የሁለትዮሽ ግንኙነት በሻከረበተ ወቅት የሚደረግ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው÷ ፕሬዚዳንት ሺ ጂን ፒንግ በሳዑዲ ዓረቢያ የሚያደርጉት የስራ ጉብኝት ሀገራቱ ያላቸውን ታሪካዊ እና ስትራቴጂካዊ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ ነው፡፡

ፕሬዚዳንቱ በሳዑዲ ቆይታቸውም 14 የዓረብ ሀገራት በሚሳተፉበት የመጀመሪያው የቻይና -ዓረብ ስብሰባ ላይ እንደሚተፉ ይጠበቃል፡፡

ይህም ቤጂንግ ከዓረብ ሀገራ ጋር ያላትን ግንኙነት ይበልጥ ለማሳደግ ለያዘቸው እቅድ የመሰረት ድንጋይ የሚጥል ነው ተብሏል፡፡

በተጨማሪም ሺ ጂንፒንግ ከሳዑዲ ዓረቢያው ንጉስ ሠልማን ቢን አብዱል አዚዝ አል ስዑድ ጋር በመምከር የ29 ቢሊየን ዶላር ስምምነት እንደሚፈራረሙ ተገልጿል፡፡

ቻይና በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የነዳጅ ዘይት ላኪ ከሆነችው ሳዑዲ ዓረቢያ ጋር ያላት ግንኙነት መጠናከርም በቀጠናው አዲስ ለውጥ ሊያመጣ እንደሚችል ሲ ጂ ቲ ኤን በዘገባው አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.