Fana: At a Speed of Life!

ነገ ለሚከበረው የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ዝግጅት መጠናቀቁን አቶ ደስታ ሌዳሞ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ነገ በሐዋሳ ከተማ ለሚከበረው የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ዝግጅት መጠናቀቁን የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ደስታ ሌዳሞ ገለጹ፡፡

17ኛው የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን ከፌዴራል እና ከተለያዩ ክልሎች የተውጣጡ ተወካዮች በተገኙበት ነገ በሐዋሳ ከተማ ስታዲየም ይከበራል፡፡

የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ እንደገለጹት÷ ቀኑ ዜጎች የጋራ ጉዳያቸውን በሚመለከት በፌዴራል ስርዓት የሚተዳደሩበትና በየአካባቢያቸው ራሳቸውን የሚያስተዳደሩበትን ነፃነት ያቀዳጃቸው ነው።

በዓሉ ማንነታችንና መልካምነታችንን የምናሳይበት፣ ከሌሎች ወንድምና እህቶቻችን ጋር ይበልጥ የምንተዋወቅበት በመሆኑ ባማረና በተሳካ ሁኔታ ለማክበር የሚያስችል ዝግጅት ተጠናቋል ሲሉ ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

ህብረተሰቡ በዓሉን ለማክበር ወደ ክልሉ የሚመጡ እንግዶቹንና የተለያዩ ብሔር፣ ብሔረሰቦችን በአክብሮት እሴት ተቀብሎ እንዲያስተናግድ ጥሪ አቅርበዋል።

የሐዋሳ ከተማና አካባቢው ሕዝብም በእለቱ በነቂስ በመሳተፍ ከእንግዶች ጋር በአንድነት በዓሉን በደማቅ ሥነ ስርዓት እንዲያከብር መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.