Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ አምስት አባላት ያሉት የፀረ ሙስና ኮሚቴ አቋቋሙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ አምስት አባላት ያሉት የፀ ሙስና ኮሚቴ አቋቋሙ፡፡

የጸረ ሙስና ኮሚቴ አባላቱም÷ ወ/ሮ ሊድያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ፣ አቶ ጀማል ረዲ የአዲስ አበባ ከተማ የፀረ ሙና ኮሚሽን ኮሚሽነር፣ አቶ ተስፋዬ ደጀኔ የአዲስ አበባ ከተማ የፍትህ ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ፣ አቶ ጥላሁን ግድየለው የአዲስ አበባ ከተማ አቃቤ ህግ እና ኮ/ር አህመድ መሃመድ የገቢዎች ቢሮ ም/ቢሮ/ ኃላፊ ናቸው፡፡

ህብረተሰቡ በ 9977 የነፃ የስልክ መስመር አስፈላጊውን ጥቆማና መረጃ በመስጠት ለፀረ ሙስና ትግሉ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ በማድረግ ከኮሚቴው ጎን እንዲቆም የከተማ አስተዳደሩ ጥሪ አቅርቧል፡፡

የተጀመረውን የፀረ ሙስና ንቅናቄ ለመግታትና ለማሰናከል በማሰብ የተለያዩ አጀንዳዎችን በመፍጠርና በተለይ ትምህርት ቤትን የሁከት ማእከል ለማድረግ በከተማችን የተደራጀ ቡድን እንቅስቃሴ ውስጥ ገብቷል ብሏል ከተማ አስተዳደሩ፡፡

ሕዝቡም ይህን አውቆ በንቃት በመከታተል ይህንን ሴራ እንዲያከሽፍና የፀረ ሌብነት ትግሉ የማይቋረጥ መሆኑን በመገንዘብ ለኮሚቴው አስፈላጊውን ማስረጃና ጥቆማ እንዲያቀርብና ትግሉን ከጫፍ እንዲያደርስ ጥሪ መቅረቡን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.