Fana: At a Speed of Life!

ለኦሮሚያ ክልል 900 የውኃ መሳቢያ ፓምፖች ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስኖና ቆላ አካባቢ ሚኒስቴር ለኦሮሚያ ክልል 900 የውኃ መሳቢያ ፓምፖች ድጋፍ አደረገ፡፡

የውኃ መሳቢያ ፓምፖቹን የመስኖና ቆላ አካባቢ ሚኒስትር አይሻ መሐመድ ለኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ አስረክበዋል፡፡

ኢንጂኒየር አይሻ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት የውኃ መሳቢያ ፓምፖቹ ክልሉ እያከናወነ ላለው የበጋ የስንዴ ልማት ትልቅ እገዛ እንደሚያደርጉ እና ድጋፉም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡

አቶ ሽመልስ አብዲሳ ለተደረገው ድጋፍ አመስግነው የውኃ መሳቢያ ፓምፖቹ ለአርሶ አደሩና አርብቶ አደሩ ትልቅ ትርጉም ያላቸውና ሕይወት የሚቀይሩ ናቸው ብለዋል፡፡

በሚኒስቴሩ የመስኖ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ብርሃኑ ሌንጂሶ ሚኒስቴሩ 4 ሺህ ያህል የውኃ መሳቢያ ፓምፖችን ለሁሉም ክልሎችና ለሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች አቅርቧል ማለታቸው የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.