Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ከኖርዌ ዓለም አቀፍ የልማት ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የኖርዌ ዓለም አቀፍ የልማት ሚኒስትር አን ቤት ቲቪንሪምን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ፡፡

አን ቤት ቲቪንሪምን በሶማሌ እና ኦሮሚያ ክልሎች በተመድ በአደጋ ጊዜ ስለሚኖር የትምርህት ሁኔታ ዓለም አቀፍ ፈንድ እና በኖርዌ ሚሽን የተሠሩ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል፡፡

ከጉብኝታቸው በኋላም÷ ስለጉብኝቱ ዓላማ፣ በክልሎቹ ስለጎበኟቸው ትምህርት ቤቶች፣ ስለ ሴት ተማሪዎች ሁኔታ፣ ስላዩአቸው ተስፋ ሰጪ ለውጦችና የኖርዌይ መንግሥት የልማት ዕቅዶችን ለፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ አብራተዋል፡፡

ኖርዌ ከኢትዮጵያ ጋር አብራ ለመሥራት ቁርጠኛ መሆኗንም አረጋግጠዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.