Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ሩሲያ ኢኮኖሚያዊ ትብብራቸውን ለማሳደግ በቁርጠኝነት እንደሚሠሩ አስታወቁ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና ሩሲያ ኢኮኖሚያዊ ትብብራቸውን ለማሳደግ በቁርጠኝነት እንደሚሠሩ አስታወቁ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የሩሲያ ፌዴሬሽን ልዑካን ቡድን በኢትዮ-ሩሲያ የጋራ ሚኒስትሮች ኮሚሽን መሪ የሆኑትን ኤቭጄኒ ፔትሮቭን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

አቶ ደመቀ መኮንን ሩሲያ በበርካታ ዓለምአቀፋዊ መድረኮች ለኢትዮጵያ ስታደርግ ለነበረው ያላሰለሰ ድጋፍ ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል፡፡

የሩሲያ ኢንቨስተሮችም በኢትዮጵያ መዋዕለ-ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ግብዣ አቅርበውላቸዋል፡፡

ኤቭጄኒ ፔትሮቭ በበኩላቸው ሩሲያ ለኢትዮጵያ የተለየ ቦታ እንዳላት ገልጸዋል፡፡

ሀገራቱ ለዓመታት ጠንካራ ፖለቲካዊ ፣ ባሕላዊ፣ እና ዲፕሎማሲያዊ ትስስሮች ማዳበራቸውንም ኤቭጄኒ ማስታወሳቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.