Fana: At a Speed of Life!

የሩሲያ ኤምባሲ የተለያዩ ይዘት ያላቸውን መፃሕፍት ለአብርሆት ቤተ መፃሕፍት አበረከተ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 29፣ 2015፣ (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ የተለያዩ ይዘት ያላቸውን መፃሕፍት ለአብርሆት ቤተ መፃሕፍት አበረከተ።

በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር  ኢቪግኒ ተርዮክኢን  ጨምሮ ሌሎች የኤምባሲው ተወካዮች በተገኙበት መፃሕፍቶቹ ለአብርሆት ቤተ መፃሕፍት ተበርክተዋል።

የተበረከቱት መጽሃፍት በሩሲያ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የተሰባሰቡ መፃሕፍት መሆናቸው ነው የተገለፀው።

አምባሳደሩ በሁለገቡ የአብርሆት ቤተ መፃሕፍት ባደረጉት ጉብኝት ልዩ ልዩ ይዘት ያላቸውን መፃሕፍት ኤምባሴያቸው በመለገሱ መደሰታቸውን ገልጸዋል።

ለሁሉም ጉዳዮች ቁልፍ መሳሪያ ለሆነው ትምህርት ትኩረት በመስጠት አንባቢ ትውልድ መገንባት ወሳኝ መሆኑን እና
በተለይም አብርሆት ቤተመፃሕፍት የልጆች ማንበቢያ ክፍል መኖሩ ታዳጊዎች መፃሕፍት እንዲያነቡ፣ የዕይታ አድማሳቸው እንዲሰፋና ዓለምን እንዲገነዘቡ ያስችላቸዋል ነው ያሉት።

በእለቱ  የቤተመፃሕፍቱ ዋና ዳይሬክተር ውብዓየሁ ማሞ ስለተደረገው ድጋፍ አመስግነው መፃሕፍቶቹን ተረክበዋል።

በተጨማሪም ዳይሬክተሩ ምክንያታዊና መረጃ ያለው ትውልድ ለመገንባት ሀገር በቀል መፃሕፍቶችን ብቻ ሳይሆን እንደዚህ ያሉ አለም አቀፍ ይዘት ያላቸዉ መፃሕፍት ያሰፈልጋሉ ማለታቸውን ከቤተፃሕፍቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.