Fana: At a Speed of Life!

17ኛው የብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል በሀዋሳ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 17ኛው የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል በሀዋሳ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው፡፡

በዓሉ “ሕብረ ብሔራዊ አንድነት ለዘላቂ ሰላም!” በሚል መሪ ቃል ነው በሀዋሳ ስታዲየም በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ የሚገኘው፡፡

በአከባበር ስነ ስርዓቱ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ ሚኒስትሮች፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እና ሌሎች የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች ታድመዋል፡፡

በተጨማሪም በሺህዎች የሚቆጠሩ የተለያዩ ብሔሮች እና ብሔረሰቦች ተወካዮች፣ የከተማዋ ነዋሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በክብረ በዓሉ ላይ የተለያዩ ብሔር፣ ብሄረሰቦች ባህላቸውን፣ ትውፊታቸውን እና ማንነታቸውን የሚያንጸባርቁ ትዕይንቶችን አቅርበዋል፡፡

የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዋንጫ ለአንድ ዓመት ያህል በኦሮሚያ ክልል በነበረው ቆይታ 1ቢሊየን 50 ሚሊየ ብር መሰብሰቡ ተገልጿል፡፡

ዋንጫውን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን አማካኝነት የኦሮሚያ ክልል ለሲዳማ ክልል አስረክቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.