Fana: At a Speed of Life!

ዋልታ ረገጥ አስተሳሰብና ፖለቲካን መሸቀጥ ኢትዮጵያን ጉልበት የሚያሳጣት ብቻ ሳይሆን የሚበትን የአንድነት ፀር ነው – ዶ/ር ለገሰ ቱሉ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዋልታ ረገጥ አስተሳሰብ እና ፖለቲካን መሸቀጥ ኢትዮጵያን ጉልበት የሚያሳጣት ብቻ ሳይሆን የሚበትን የአንድነት ፀር ነው ሲሉ የመንግስት ኮሙኑኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ ገለጹ፡፡

ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ሕብረ ብሔራዊ አንድነት ለዘላቂ ሰላም፤ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ብቸኛው መፍትሄ ነው ብለዋል።

ዋልታ ረገጥ አስተሳሰብ እና ፖለቲካን መሸቀጥ ኢትዮጵያን ጉልበት የሚያሳጣት ብቻ ሳይሆን የሚበትን የአንድነት ፀር ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡

እዚያም እዚህ እየተፈጠሩ ያሉ ችግሮች መነሻቸውም ሆነ መድረሻቸው ኢትዮጵያን የማፍረስ ተልዕኮን ባነገቡ፣ ፖለቲካን እንደሸቀጥ የሚጠቀሙ የውስጥ ባንዳዎች ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር በጣምራ የሚያካሄዱት የቀደመውን ዘመቻ የማስቀጠል ፍላጎት መሆኑንም አስረድተዋል።

መስሏቸው ይሆናል እንጂ ይህ መቼም ቢሆን አይሳካም ያሉት ሚኒስትሩ÷ ይህን እኩይ ሴራ ለማክሸፍ በሚደረገው እንቅስቃሴ መላ ህዝባችን እንደቀደመው ሁሉ በጋራ መቆም አለበት ብለዋል።

ጊዜው በሕብረ ብሔራዊ አንድነት የኢትዮጵያን ችግሮች በጋራ የምንፈታበት፣ የሁላችንም ጥረትና ትጋት የሚጠይቅ ነው ሲሉም አጽንት ሰጥተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.