Fana: At a Speed of Life!

1ሺህ 20 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)  በሶስት ዙር በተከናወነ በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ ያሉ ዜጎችን የመመለስ ስራ 1ሺህ 20 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ መቻሉ ተገልጿል፡፡

በዚህም ወደ ሀገራቸው ከተመለሱ ዜጎች መካከል አስራ አንዱ እድሜያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች መሆናቸው ታውቋል፡፡

ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማእከላት እንዲሄዱ መደረጉን ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከሕዳር 12 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን በተከናወነ ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ 8 ሺህ 988 ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል ነው የተባለው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.