Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ከአውሮፓ ኅብረት የውጪ ጉዳይና የደኅንነት ፖሊሲ ከፍተኛ ተወካይና የኅብረቱ ኮሚሽን ም/ፕሬዚደንት ጆሴፍ ቦሬል ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከአውሮፓ ኅብረት የውጪ ጉዳይና የደኅንነት ፖሊሲ ከፍተኛ ተወካይና የኅብረቱ ኮሚሽን ምክትል ፕሬዚደንት ጆሴፍ ቦሬል ጋር በስልክ ተወያዩ።

በውይይታቸውም አፍሪካ እና አውሮፓ በኮሮናቫይረስ (ኮቪድ19) ምክንያት የተጋፈጡትን የጋራ ፈተና አስመልክቶ መምከራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በፌስቡክ ገፃቸው ባወጡት መረጃ አስታውቀዋል።

በተጨማሪም በውይይታቸው ኮሮናቫይረስ (ኮቪድ19) አስከፊ የጤና ቀውስ ከማድረሱ በፊት በአያሌ መንገዶች አብሮ በመሥራት አደጋውን ለመቀልበስ መስማማታቸውንም ገልፀዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.