Fana: At a Speed of Life!

በሀዋሳ የተከበረው የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በሰላም ተጠናቋል- የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልል አስተናጋጅነት ዛሬ የተከበረው 17ኛው የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ያለምንም የጸጥታ ችግር በሰላም መጠናቀቁን የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ።
 
የክልልና የፌዴራል የጸጥታ መዋቅር ከአካባቢው ወጣቶችና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችን ያሳተፈና የተቀናጀ የጸጥታ ስራ ሲያከናውን መቆየቱን የቢሮው ሃላፊ አቶ አለማየሁ ጥሞቲዮስ ለኢዜአ ገልጸዋል።
 
በዚህም የበዓሉ ሂደት ያለምንም የጸጥታ ችግር በተሰካ ሁኔታ ተከብሮ መጠናቀቁን አስታውቀዋል።
 
በዓሉ በሰላም ተክብሮ እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላደረጉ የጸጥታ አካላትና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ምስጋና አቅርበዋል።
 
በዓሉን ለማክበር ከመላው የሀገሪቱ ክፍል የመጡ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ተወካዮች እስኪመለሱ ድረስ በተለመደው መልካም መስተንግዶ በማቆየት ለመሸኘት ዝግጅት መደረጉንምኢዜአ ዘግቧል፡፡
 
በሲዳማ ክልል አስተናጋጅነት ዛሬ በሀዋሳ በድምቀት በተከበረው 17ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌደራልና የክልሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ታድመዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.