Fana: At a Speed of Life!

ሉዊስ ኤነሪኬ ከስፔን ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝነታቸው ተሰናበቱ

አዲስ አበባ፣ህዳር 29፣2015 (ኤፍ ቢሲ) ሉዊስ ኤነሪኬ ከስፔን ብሄራዊ አሰልጣኝነታቸው መሰናበታቸውን የስፔን እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡

ስፔን በኳታሩ የዓለም ዋንጫ በሞሮኮ በመለያ ምት መሸንፏን ተክትሎ ነው ፌዴሬሽኑ ሉዊስ ኤነሪኬን ከብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝነቱ የተሰናበተው።

አሰልጣኙ እና የቡድን አጋሮቻቸው ብሄራዊ ቡድኑን በመምራት ላበረከቱት አስተዋፅኦ የስፔን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

በ2018 ሰፔን ብሄራዊ ቡድንን የተረከቡት ሉዊስ ኤንሪኬ በቆይታቸው በአወሮፓ ኔሽንስ ሊግ  አራት ጨዋታዎችን ማለፍ የቻሉ ሲሆን፥ በዩሮ 2020 ከብሄራዊ ቡድኑ ጋር ለግማሽ ፍፃሜ መድረስ ችለዋል፡፡

በባርሴሎና ስኬታማ ጊዜን ያሳለፉት ኤነሪኬ ከ2014 እሰከ 2017 ባለው ጊዜ የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን፣ ሁለት የላሊጋ ዋንጫዎች ፣ ሶስት የኮፓ ዴል ሬይ ዋንጫዎች ፣ የሱፐር ካፕ ፣ የክለቦች ዋንጫ እና የስፓኒሽ ሱፐር ካፕ ዋንጫዎችን ማንሳት ችለዋል፡፡

አሰልጣኝ ሉዊስ ኤነሪኬ ለወጣት ተጫዎቾች እድል በመሰጠት የሚታወቁ እና አሁን ያለውን የሰፔን ብሄራዊ ቡድን በመገንባት ረገድ ከፍተኛ ሚና መጫወታቸውን ዘጋርዲያን ስፖርት ዘግቧል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.