Fana: At a Speed of Life!

ፈረንሳይ በ1960ዎቹ ከኢትዮጵያ በውሰት የወሰደቻቸውን 740 ቅርሶች መለሰች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፈረንሳይ በ1960ዎቹ ከኢትዮጵያ በውሰት የወሰደቻቸውን 740 ቅርሶች በመመለስ ዛሬ ለኢትዮጵያ ቅርስ ጥናት ባለስልጣን አስረክባለች።

ቅርሶቹ ከ10 ሺህ እስከ ሁለት ሚሊየን ዓመት ድረስ ያስቆጠሩ ናቸው፡፡

እርክክቡ በኢትዮጵያ የፈረንሳይ ኤምባሲ የትብብር ኃላፊ ሶፊ ማካሜ እና የኢትዮጵያ ቅርስ ጥናት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አበባው አያሌው በተገኙበት ነው የተከናወነው፡፡

ረዳት ፕሮፌሰር አበባው በዚሁ ወቅት እንደገለጹት÷ ተመላሽ የሆኑት ቅርሶች  የእንስሳትና የድንጋይ መሳሪያዎች  እንዲሁም የእንስሳት ቅሪተ አካል ናቸው።

ቅርሶቹ በፈረንሳዩ ተመራማሪ ዦን ሻቫዩ አማካይነት በመልካ ቁንጥሬና በኦሞ አካባቢ የተገኙ ሲሆን÷ በ1960ዎቹ ወደ ፈረንሳይ ለተጨማሪ ጥናት በውሰት የሄዱ መሆናቸውንምተናግረዋል፡፡

ሶፊ ማካሜ የተመለሱ ቅርሶች ብዛት 740 መሆናቸውን ጠቅሰው ከእነዚህ መካከል 28ቱ የእንስሳት ቅሪተ አካል መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያና ፈረንሳይ በቅርስ ጉዳዮች ያላቸውን መልካም ትብብር  አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.