Fana: At a Speed of Life!

በምእራብ ኦሮሚያ በሚገኙ ዞኖች ተቋርጦ የነበረው የቴሌኮም አገልግሎት ዳግም እንዲጀምር መደረጉን የክልሉ መንግስት ገለፀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በምእራብ ኦሮሚያ በሚገኙ ዞኖች ውስጥ በተወሰኑ አካባቢዎች ላይ ተቋርጦ የነበረው የቴሌኮም አገልግሎት ዳግም እንዲጀምር መደረጉን የክልሉ መንግስት ገለፀ።

የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ፥ በአካባቢዎቹ የቴሌኮም አገልግሎት ዳግም ወደ ስራ እንዲመለስ የክልሉ መንግስት እና የፌደራል መንግስት በጋራ ሲሰሩት የነበረው ስራ መጠናቀቁን አስታውቀዋል።

ይህንን ተከትሎም ከዛሬ ጀምሮ በምእራብ ኦሮሚያ በሚገኙ ዞኖች ውስጥ በተወሰኑ አካባቢዎች ላይ ተቋርጦ የነበረው የቴሌኮም አገልግሎት ዳግም አገልፍሎት እንዲጀምር ተወስኗል ብለዋል።

አቶ ሽመልስ በመግለጫቸው አክለውም፥ ባለፉት ቀናቶች በቄለም ወለጋ፣ ምእራብ እና ምስራቅ ወለጋ እንዲሁም ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ባደረጉት ጉብኝት አካባቢዎቹ ወደ ሰላም እና መረጋጋት መመለሱን ገልጸዋል።

አሁን የተረጋገጠውን ሰላምና መረጋጋት ተከትሎም ግንባታቸው ተቋርጦ የቆዩትፕሮጀክቶች ወደ ስራ እንዲገቡ መደረጉን በማንሳት፤ አዳዲስ የሚጀመሩትም ወደ ስራ እንዲገቡ ጥረቶች ይቀጥላሉ ብለዋል።

ለተመዘገበው ሠላምም ህዝቡ ለተጫወተው ሚናም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.