Fana: At a Speed of Life!

በአክራሪነት እና ሽብርተኝነት ላይ ከተናጠል ይልቅ በጋራ እርምጃ መውሰድ ይገባል – አምባሳደር ብርቱካን አያኖ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ አፍሪካ በአክራሪነት እና በሽብርተኝነት ላይ ከተናጠል ይልቅ በጋራ እርምጃ ልትወስድ እንደሚገባ ገለጹ፡፡

በአልጄሪያ ኦራን ከተማ 9ኛው ከፍተኛ የአፍሪካ ሠላምና ፀጥታ ጉባዔ እየተካሔደ ነው፡፡

በጉባዔው ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ባደረጉት ንግግር÷ የአክራሪነት እና የሽብርተኝነት ተግዳሮቶችን በብቸኝነት መቋቋም የማይቻል በመሆኑ የጋራ እርምጃ አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሽብርተኝነትን ለመዋጋትና ለሚደረጉ የሰላም እንቅስቃሴዎች ቁርጠኛ ነች ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.