Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ የአፍሪካ ቀዳማዊ እመቤቶች የልማት ድርጅት ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የአፍሪካ ቀዳማዊ እመቤቶች የልማት ድርጅት የወቅቱ ፕሬዚዳንት የሆኑትን የናሚቢያ ቀዳማዊት እመቤት ሞኒካ ጊንጎስ በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።

በውይይታቸውም በአፍሪካ የሴቶችን አመራርነት ሚና ማጎልበትና የሴት መሪዎችን ብዛት ማሳደግ ላይ መምከራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በአፍሪካ የሴቶችን የመሪነት አቅም መጠቀምና የመሪዎችን ቁጥር ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ እንዲሁም የሴቶችን የሙያ፣ የክህሎትና የመሪነት ሚና ለማጠናከር በጋራ መሥራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይም መክረዋል፡፡

የአፍሪካ ሴት መሪዎች ጥምረትን ጨምሮ በአህጉሪቷ ያሉ የሴት አደረጃጀቶች ጋር በጋራ እንደሚሠሩም በውይይታቸው ተመላክቷል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.