Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል የሽረ ከተማ የኤሌክትሪክ አገልግሎት አገኘች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአንድ ዓመት በላይ የኤሌክትሪክ አገልግሎት የተቋረጠባት ሽረ ዳግም የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማግኘቷን ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡

ሁመራ እና አካባቢውም የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማግኘት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

በአገልግሎቱ የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር መላኩ ታዬ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ ሙሉ በሙሉ ወድሞ የነበረው የሽረ ኤሌክትሪክ መሰረት ልማት ተጠግኖ ምሽቱን ሽረ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ዳግም አግኝታለች፡፡

አገልግሎቱ ዳግም እንዲጀምር አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በተመሳሳይ ሁመራ እና አካባቢው አገልግሎቱን ዳግም እንዲያገኙ የጥገናና እና ፍተሻሥራው መጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡

በዚሁ መሰረት ከተቻለ ምሽቱን ካልሆነም ነገ የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲያገኙ ባለሙያዎች ርብርብ እያደረጉ መሆንም ገልጸዋል፡፡

በትግራይ ክልል ያሉ ከተሞችም አገልግሎት እንዲያገኙ የቴክኒክ ኮሚቴ መቋቋሙንና ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.