Fana: At a Speed of Life!

ምርጫ ቦርድ የዲጂታል መረጃ ዝግጅትን በሙከራ ደረጃ አስተዋወቀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ6ኛው አጠቃላይ ምርጫን የመራጮች መዝገብ በሙከራ ደረጃ የማዘመንና ኦዲት ማድረግ ስራ ዛሬ በይፋ አስጀምሯል።

አንድ ዓመት የፈጀው ይህ የዲጂታል ምዝገባ ቴክኖሎጂ በ6ኛው ብሔራዊ ምርጫ የተመዘገቡ መራጮችን መረጃ ከወረቀት ወደ ዲጂታል በመቀየር ነው ስራውን የጀመረው።

በመቀጠልም ምርጫውን ኦዲት ማድረግ እንደሚጀመር ተገልጿል፡፡

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ውብሸት አየለ÷ የዲጂታል ምዝገባው የምርጫ ስርዓቱን የሚያዘምን እንደሆነ ገልጸዋል።

ይህ ቴክኖሎጂ እንዲሳካም የአውሮፓ ህብረትና የጀርመን መንግስት የገንዘብ ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን÷ ዩ ኤን ዲ ፒ ደግሞ ለባለሙያዎች ሙያዊ ድጋፍ መስጠታቸው ተጠቅሷል።

የዲጂታል መረጃ ዝግጅቱ መረጃዎችን በአስተማማኝ ሁኔታ ለመያዝና በሚፈለጉበትም ወቅት በቀላሉ ለማግኘት የሚያስችል ነው ተብሏል።

በዘመን በየነ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.