Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ማንኛውም የቋሚ ንብረት ስም ዝውውር አገልግሎት በጊዜያዊነት ታገደ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማንኛውም የቋሚ ንብረት ስም ዝውውር አገልግሎት በጊዜያዊነት መታገዱን የከንቲባ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡
 
በከንቲባ ጽህፈት ቤት የካቢኔ ጉዳዮች ዘርፍ ሃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፥ በአዲስ አበባ ከተማ ከሕዳር 29 ቀን 2015 ጀምሮ ማንኛውም የቋሚ ንብረት ስም ዝውውር አገልግሎት በጊዜያዊነት ታግዷል፡፡
 
አገልግሎቱ የታገደው በከተማዋ ህገ ወጥነትን ለመከላከል እየተደረገ ያለውን ሒደት ውጤታማ ለማድረግ መሆኑን ሃላፊው ተናግረዋል፡፡
 
ለሁሉም ክፍለ ከተሞች እና ለሚመለከታቸው አካላትም የተላለፋው ውሳኔ ተፈጻሚ እንዲሆን ትዕዛዝ መተላለፉን ነው የገለጹት፡፡
 
በመላኩ ገድፍ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.