Fana: At a Speed of Life!

ብልጽግና ፓርቲ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔውን እያካሔደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ብልጽግና ፓርቲ 1ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔውን በሐዋሳ ከተማ በማካሔድ ላይ ነው፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ አባላት፣ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት እንዲሁም በተለያየ ፓርቲያዊ መዋቅር ውስጥ የሚገኙ አመራሮች በተገኙበት ነው አስቸኳይ ጉባዔው እየተካሔደ የሚገኘው፡፡

ጉባዔውን በአስቸኳይ ማካሔድ ያስፈለገው ባለፈው መጋቢት ወር ፓርቲው ባካሔደው የመጀመሪያ ጉባዔ በምርጫ ቦርድ ያልተሟሉ አንዳአንድ ነጥቦች እንዲታረሙ በተቀመጡ አቅጣጫዎች መሰረት መሆኑን  የብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

በመሆኑም ፓርቲው የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን የማስተካከያ ትዕዛዝ በመቀበል ጉዳዩ የሚመለከታቸውን አካላት ጋብዞ ጉባዔውን ማካሔድ መጀመሩ ተመላክቷል፡፡

ፓርቲው ይህን አስቸኳይ ጉባዔ ማካሄዱ ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች እንደሚያስገኙለት እና እንደ ፓርቲም ዴሞክራሲን ለመገንባት ያለው ቁርጠኝነት በሕዝብ ዘንድ አመኔታ የሚያተርፍለት ይሆናል ነው የተባለው፡፡

በተጨማሪም በብልጽግና ፓርቲ መሪነት የተጀመረው የተቋም ግንባታ ሐሳብ ተጠናክሮ እንዲቀጠል ፓርቲው  ሁነኛ ምሳሌ መሆን እንደሚችልና ለሌሎች ፓርቲዎች ጭምር አርዓያ የሚሆን ተግባር መፈፀሙ በሚገባ ታምኖበታል ብሏል ፓርቲው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.