Fana: At a Speed of Life!

በሰላም ስምምነቱ ዙሪያ በሀድሰን ኢንስቲትዩት ለሚመለከታቸው አካላት ማብራሪያ ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰላም ስምምነቱ እና መልሶ ግንባታ ዙሪያ በሀድሰን ኢንስቲትዩት በመገኘት ለሚመለከታቸው አካላት ማብራሪያ መሰጠቱን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ገለጹ፡፡
 
አምባሳደር ሬድዋን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ፥ በኢትዮጵያ መንግስትና ህወሓት መካከል በተደረሰው የሰላም ስምምነት ዙሪያ ከሚለከታቸው ተጋባዥ እንግዶች ጋር ፍሬማ ውይይት መደረጉን ተናግረዋል፡፡
 
በውይይቱም በሰላም ስምምነቱ፣በመልሶ ግንባታ እና ማቋቋም ስራዎች ላይ አስፈላጊው ማብራሪያ መሰጠቱን ጠቁመዋል፡፡
 
ተቀማጭነቱን ዋሽንግተን ዲሲ ያደረገው ሀድሰን ኢንስቲትዩት በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ምሁራንን እና ውሳኔ ሰጪ ፖለቲከኞችን በማገናኘት የሚያወያይ ተቋም ነው።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.