Fana: At a Speed of Life!

ፖሊስ ከ26 ሺህ ዶላር በላይ ሲያዘዋውር ደርሼበታለሁ ያለውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አዋለ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ በሕገ ወጥ መንገድ 26 ሺህ 400 የአሜሪካ ዶላር ሲያዘዋውር ደርሼበታለሁ ያለውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ።

የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዋና ሳጅን ጀማል አሕመድ እንደገለጹት÷ ግለሰቡ ትናንት ምሽት 2 ሰዓት ተኩል ላይ ነው በሕግ ቁጥጥር ስር የዋው፡፡

ግለሰቡ ከአዲስ አበባ ወደ ጅግጅጋ ከተማ በአነስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በስውር ቦታ የውጭ ሀገር ገንዘብ ደብቆ በመጓዝ ላይ ሳለ በፍተሻ በቁጥጥር መዋሉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ግለሰቡ ከነ ገንዘቡ በቁጥጥር ስር የዋለው ቱሉ ዲምቱ የፍጥነት መግቢያ ኬላን አልፎ ለማምለጥ ሲሞክር በአዲስ-አዳማ የፍጥነት መንገድ ተቆጣጣሪ ፖሊሶች መሆኑ ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.