Fana: At a Speed of Life!

ለሊሴ ነሜ በአፍሪካ ልማት ባንክ የምስራቅ አፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ በአፍሪካ ልማት ባንክ የምስራቅ አፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር አብዱል ካማራ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮምሽን እና በአፍሪካ ልማት ባንክ መካከል ያለውን ግንኙነት ማጠናከል ስለሚቻልባቸው መንገዶች ላይ መምከራቸውን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

አፍሪካን ለአፍሪካውያን በተሰኘው እንቅስቃሴ ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት ለአፍሪካ ለማምጣት እና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽንን አቅም በማጎልበት የኢትዮጵያን ኢንቨስትመንት ካባቢ እና የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰትን ለማሳደግ እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.